'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን አጡት። አንድ ሰውዬ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለርሱ ሁኔታ አጣርቼ አሳውቆታለሁ።" አለና ሣቢት ጋር ሲመጣ አንገቱን አቀርቅሮ ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብሎ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" አለው። ሣቢትም 'መጥፎ ነው' ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላ…

