የትንሳኤ ቀን አንድ ሰውዬ ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል። የሆዱ አንጀትም ይዘረገፋል። አህያ በወፍጮው እንደሚሽከረከረውም የተዘረገፈውን አንጀት ይዞ ይሽከረከራል።
ከኡሳማ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉት: «ዑሥማን ዘንድ ገብተህ አታናግረውምን?» ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም አላቸው: «እናንተ በምትሰሙበት መልኩ ካልሆነ በቀር የማላናግረው ይመስላችኋልን? በአላህ እምላለሁ (መሪን በግልፅ የመቃወምን በር) ሳልከፍት በኔና በርሱ መካከል ማንም ሳይኖር አናግሬዋለሁ። የመጀመሪያው የፊትና በር ከፋች መሆንንም አልወድም። የአላህ…

