HadeethEnc · 1.23.0
ይህ ከሰባ አመት ጀምሮ እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ነው። እርሱም እሳት ውስጥ ወደ ጥልቀቷ መጨረሻ ዛሬ እስኪደርስ ድረስ እየተምዘገዘገ ነበር።" አሉ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለን ድንገት አስደንጋጭ ድምፅ ሰሙ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሉ። እኛም "አላህና መልክተኛው አዋቂዎች ናቸው።" አልን። እርሳቸውም " ይህ ከሰባ አመት ጀምሮ እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ነው። እርሱም እሳት ውስጥ ወደ ጥልቀቷ መጨረሻ ዛሬ እስኪደርስ ድረስ እየተምዘገዘገ ነበር።" አሉ።»
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሆነ ነገር ሲወድቅ የሚሰማውን አይነት አስደንጋጭ ድምፅ ሰሙ። እርሳቸው ዘንድ ያሉትንም ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ስለዚህ ድምፅ ምንነት ጠየቋቸው። ሶሐቦቹም "አላህና መልክተኛው አዋቂዎች ናቸው።" አሉ።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: ይህ የሰማችሁት ድምፅ ከሰባ አመት ጀምሮ ከጀሀነም ጫፍ የተወረወረ ድንጋይ ነው። ድምፁን በሰማችሁበት ጊዜ ወደ መጨረሻ ጥልቀቷ እስከደረሰበት የዛሬዋ ቀን ድረስ እየወረደና እየተምዘገዘገ ነበር።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: ይህ የሰማችሁት ድምፅ ከሰባ አመት ጀምሮ ከጀሀነም ጫፍ የተወረወረ ድንጋይ ነው። ድምፁን በሰማችሁበት ጊዜ ወደ መጨረሻ ጥልቀቷ እስከደረሰበት የዛሬዋ ቀን ድረስ እየወረደና እየተምዘገዘገ ነበር።
03
Benefits
መልካም ስራ በመስራትና ከጀሀነም በመጠንቀቅ ለመጨረሻው ቀን መዘጋጀት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
የሰው ልጅ የማያውቀው በሆኑ ነገሮች እውቀትን ወደ አላህ ማስጠጋቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።
አስተማሪ የሆነ ሰው ለማስረዳት የበለጠ እንዲያግዘው ከማብራራቱ በፊት ትኩረትንና ንቃትን ማነሳሳት እንደሚገባው እንረዳለን።
የሰው ልጅ የማያውቀው በሆኑ ነገሮች እውቀትን ወደ አላህ ማስጠጋቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።
አስተማሪ የሆነ ሰው ለማስረዳት የበለጠ እንዲያግዘው ከማብራራቱ በፊት ትኩረትንና ንቃትን ማነሳሳት እንደሚገባው እንረዳለን።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares