ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉ…

