በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው።
ከሙዓዝ ቢን ጀበል - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝንና ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ይንገሩኝ። አልኳቸው። እርሳቸውም: "በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የ…

