በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ…

