ጠርጥሬያችሁ አይደለም ያስማልኳችሁ። ነገር ግን ጂብሪል መጥቶ አላህ በናንተ መላእክትን እንደሚፎካከር ስለነገረኝ ነው።› አሉ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ሙዓዊያ በመስጂድ ውስጥ ክብ በሰሩ ሰዎች ላይ መጣና "ምንድን ነው ያስቀመጣችሁ?" አላቸው። እነርሱም "የተቀመጥነው አላህን ልናወሳ ነው።" አሉ። እርሱም "በአላህ ስም ማሉልኝ ከዚህ በቀር ሌላ አላስቀመጣችሁምን?" አላቸው። እነርሱም "በአላህ እንምላለን ከርሱ በቀር ሌላ አላስቀመጠንም።" አሉ። እርሱም "ያስማልኳችሁ ጠርጥሬያችሁ ሳይሆን በኔ ደረጃ ላይ ያለ ሆኖ ከአላህ መል…

