አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ።…

