ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዑሥማን ቢን አቢል ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እንዲሁም በቂረአቴ መካከል አዘናጋኝ። በኔ ላይም ያለባብስብኛል።" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!" አሉት። እርሱም "ይህንን ፈፀምኩ አላህም አስወገደልኝ።" አለ።
Explanation
Benefits
ሰይጣን ሶላት ውስጥ በሚወሰውስ ወቅት ወደ ግራ ከመትፋት ጋር ሶስት ጊዜ "አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧኒ አርረጂም" ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሚያጋጥማቸው ችግሮች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ችግራቸውን እስኪፈቱላቸው ድረስ ወደርሳቸው እንደሚመላለሱ መገለፁን እንረዳለን።
የሶሐቦች ልብ ህያው መሆኑን እንረዳለን። ሀሳባቸው ሁሉ መጪው አለም ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

