አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) አስቦ ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም በላይ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎችን ይጽፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"
Explanation
መልካምን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ሰው ባይሰራትም እንኳ ለሱ አንድ ምንዳ ትፃፍለታለች። ከሰራት ደግሞ በስራዋ አምሳያ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ከዚያም አልፎ እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ ትባዛለች። ይህ የምንዳ ጭማሪው ቀልቡ ውስጥ ባለው ኢኽላስ፣ በጥቅሙ ወደ ሌሎች ተሻጋሪነትና በመሳሰሉት ልክ ተንተርሶ ነው ።
ኃጢዐትን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ከዚያም ለአላህ ብሎ ሳይሰራት የተዋት ሰው ለሱ አንድ ምንዳ ይጻፍለታል። ወደዛች ኃጢዐት የሚያዳርሱ መንስኤዎችን ካለመፈፀም ጋር በሌላ ነገር በመጠመዱ ሳቢያ ከተዋት ምንም ነገር አይፃፍለትም። ኃጢዐቱን መስራት ስለተሳነው ከተወ ደግሞ በሱ ላይ ያለመው ትፃፍበታለች። ከሰራት ደግሞ አንዲት ሀጢዐት ትፃፍበታለች።
Benefits
በስራዎች ላይ የኒያ አስፈላጊነትና ተፅእኖን ተረድተናል።
መልካምን ሊሰራ አስቦ ላልሰራ ሰው አላህ ለሱ ምንዳ መፃፉ የአላህን ችሮታ፣ እዝነትና መልካምነትን ያስረዳል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

