HadeethEnc · 1.23.0
ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ ሰዕድ ቢን ማሊክ ቢን ሲናን አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።"
02
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድ ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም። እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና።
03
Benefits
ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን እንረዳለን።
አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም።
ይህ ሐዲሥ በንግግርም ይሁን በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን መጉዳትና መበቀል ክልክል ለመሆኑ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።
አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም።
ይህ ሐዲሥ በንግግርም ይሁን በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን መጉዳትና መበቀል ክልክል ለመሆኑ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።
Attribution
[رواه ابن ماجه والدارقطني وغيرهما مسندًا]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

