HadeethEnc · 1.23.0
አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።"
02
Explanation
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ይሁን ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድ ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም።
እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና።
ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎችን ለሚጎዳ ሰው ጉዳት እንደሚያገኘው፤ ሰዎችን ለሚያጨናንቅም መጨናነቅ እንደሚያገኘው ዛቱ።
እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና።
ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎችን ለሚጎዳ ሰው ጉዳት እንደሚያገኘው፤ ሰዎችን ለሚያጨናንቅም መጨናነቅ እንደሚያገኘው ዛቱ።
03
Benefits
ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን እንረዳለን።
አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም።
በንግግር ወይም በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን አውቆም ይሁን ሳያውቁ መጉዳት ተከልክሏል።
ምንዳ በስራው አይነት ነው የሚሰጠው። የጎዳ ሰው አላህ ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀም አላህ ያጨናንቀዋል።
ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።

Attribution
[ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares