HadeethEnc · 1.23.0
'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አንዳችሁ ከሆዱ ውስጥ አንዳችን ነገር ያገኘ ጊዜ ከሆዱ አንዳች ነገር ወጥቷል ወይስ አልወጣም የሚለውን መለየት ካስቸገረው ድምፅ እስኪሰማ ወይም ሽታ እስኪያገኝ ድረስ (ሶላቱን አቋርጦ) ከመስጂድ አይውጣ።'"
02
Explanation
ሰጋጅ ከሆዱ ውስጥ አንዳች ነገር መውጣት አለመውጣቱን አስመልክቶ ከተጠራጠረ የፈስ ድምፅ በመስማት ወይም ጠረን በማሽተት ዉዱእ የሚያጠፋ ነገር መከሰቱን እርግጠኛ እስኪሆን ድረስ ዉዱእ ለመድገም ብሎ ሶላቱን አቋርጦ አይውጣ። የተረጋገጠ ነገር በጥርጣሬ አይበላሽምና። እሱ ዉዱእ እንደነበረው እርግጠኛ ነው። ዉዱእ ማጥፋቱ ግን አጠራጣሪ ነገር ነው።
03
Benefits
ይህ ሐዲሥ ከኢስላም መሰረቶች አንዱና ከፊቅህ መርሆዎች መካከል አንዱ መርህ ነው። እርሱም: የተረጋገጠ ነገር በጥርጣሬ አይወገድም ነው። መሰረቱ ተቃራኒው እስኪረጋገጥ ድረስ ሁሉም ነገር በነበረበት መጽናቱ ነው።
ጥርጣሬ በጦሀራ ላይ ተፅእኖ እንደማያሳድር እንረዳለን። አንድ ሰጋጅ ዉዱእ ማጥፋቱን እርግጠኛ እስካልሆነ ድረስ በዉዱኡ ላይ እንደፀና ይቆያል።
ጥርጣሬ በጦሀራ ላይ ተፅእኖ እንደማያሳድር እንረዳለን። አንድ ሰጋጅ ዉዱእ ማጥፋቱን እርግጠኛ እስካልሆነ ድረስ በዉዱኡ ላይ እንደፀና ይቆያል።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

