የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰባት ነገር አዘዙን፤ ከሰባት ነገርም ከለከሉን።
ከበራእ ቢን ዓዚብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰባት ነገር አዘዙን፤ ከሰባት ነገርም ከለከሉን። በሽተኛን በመጠየቅ፣ ጀናዛን በመሸኘት፣ ላስነጠሰ ዱዓ በማድረግ፣ መሃላን ወይም የማለን ሰው በማጥራት፣ ተበዳይን በመርዳት፣ የጠራንን ሰው ጥሪውን በማክበር፣ ሰላምታን በማስፋፋት…

