'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"
Explanation
1 - በአላህ ማጋራት፦ ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፣ ከአላህ ውጪ የሆነን አካል ከአላህ ጋር በተመላኪነቱ ወይ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ እኩል ማድረግ ማለት ነው።
2 - የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፦ ይህም ወላጆች ላይ በንግግርም ይሁን በተግባር በማንኛውም መልኩ ማወክና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው።
3 - ውሸት መናገር ነው። በውሸት መመስከርም እዚህ ውስጥ ይካተታል: ይህም ከተቀጠፈበት አካል ንብረቱን ለመውሰድ ወይም ክብሩ ላይ ወሰን ለማለፍ ወይም የመሳሰሉትን በመፈለግ የተቀጠፈና የተዋሸ ንግግር ሁሉ ማለት ነው።
ከመደጋገማቸው የተነሳ ሶሐቦች ለነቢዩ ካላቸው እዝነትና የሳቸውን መረበሽ ጠልተው ምነው ዝም ባሉ ብለው እስኪመኙ ድረስ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የውሸትን ፀያፍነት እና ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረውን መጥፎ አሻራ ለማስገንዘብ ከሐሰተኛ ቃል ደጋግመው አስጠነቀቁ።
Benefits
ሐዲሡ ላይ የወላጆች ሐቅ ከአላህ ሐቅ ጋር በመቆራኘቱ የወላጆችን ሐቅ ታላቅነት እንረዳለን።
ወንጀሎች ወደ ትላልቅና ትናንሽ ይከፈላሉ። ትላልቅ የሚባሉት: ማንኛውም አለማዊ ቅጣት የተቀመጠለት ወንጀል ለምሳሌ :- ቅጣቱ በሸሪዓዊ መቅጫ ህግ ውስጥ ያለ (ሑዱድ)፣ መረጋገም ያለበት፤ ወይም እሳት መግባትን የመሰለ አኺራዊ ዛቻ የመጣበት ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው። የክልከላ ደረጃውም ከፊሉ ከከፊሉ ይከብዳል። ትናንሽ ወንጀሎች የሚባሉት ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች ውጪ ያሉት ናቸው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

