ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ የቆሰለ ሰውዬ ነበር። ትእግስት በማጣቱም ቢላ አንስቶ እጁን ቆረጠ። እስኪሞት ድረስም ደሙ አልተቋረጠም። አላህም እንዲህ አለ: 'ባሪያዬ ነፍሱን በማውጣት ተቻኮለኝ። በርሱ ላይም ጀነትን እርም አድርጌበታለሁ።'
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከሐሰን እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ጁንዱብ ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እዚሁ መስጂድ ውስጥ ነገሩን። ከነገሩን ጀምሮም አልረሳነውም። ጁንዱብም በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ዋሽቷል ብለንም በፍፁም አንፈራም። እንዲህም አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ የቆሰለ ሰውዬ ነበር። ትእግስት በማጣቱም ቢላ አንስቶ እጁን ቆረጠ። እስኪሞት ድረስም ደሙ አልተቋረጠም። አላህም እንዲህ አለ: 'ባሪያዬ ነፍሱን በማውጣት ተቻኮለኝ። በርሱ ላይም ጀነትን እርም አድርጌበታለሁ።' "
Explanation
Benefits
ስላለፉ ህዝቦች መልካምና ትምህርት የሚወሰድበትን ነገር ማውራት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የአላህ ሐቆችን ሳይተላለፉ መቆም እንደሚገባ፤ ፍጡራንን ነፍሳቸውን ከማጥፋት በመከልከል ለነርሱ ያለውን እዝነትና ነፍሶችም የአላህ እንደሆኑ እንረዳለን።"
ነፍስን ወደ ማጥፋት የሚያመሩ ሰበቦችን ከመጠቀም መከልከሉንና ነፍስን በማጥፋት ዙሪያ ከባድ ዛቻ መምጣቱን ተረድተናል።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከሐዲሡ የምንረዳው እጁን የቆረጠው ሞትን በመፈለግ እንጂ ጥቅሙ አመዛኝ በሚሆን መልኩ ህክምናን አስቦ እንዳልነበረ ነው።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

