የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። ሽቶ ተሸካሚ ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይ ከርሱ መልካም መአዛን ታገኛለህ። ወናፍ ነፊ ደግሞ ወይ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።"
Explanation
የመጀመሪያው አይነት: ወደ አላህ የሚጠቁም፣ ወደ አላህ ውዴታ የሚመራና በአምልኮ ላይ የሚያግዝ መልካም ጓደኛ ነው። የርሱም ምሳሌ ሽቶ እንደሚሸጥ ሰው ምሳሌ ነው። ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይም ከርሱ መልካም መአዛን ታሸታለህ።
ሁለተኛው አይነት ደግሞ ከአላህ መንገድ የሚያቅብ፣ ወንጀል በመፈፀም ላይ የሚያግዝ ፣ መጥፎ ተግባራትን የምታይበት መጥፎ ጓደኛ ነው። የሱን አይነት ሰው ወዳጅና ጓደኛ አድርገህ በመያዝህም የሚያስወቅስህ ነው። የርሱም ምሳሌ ወናፍ እንደሚያናፋ ብረት ቀጥቃጭ ነው። እርሱም ወይ በሚፈነጣጠረው እሳት ልብስህን ያቃጥላል ወይም ወደርሱ በመቅረብህ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።
Benefits
የመልካምና የበጎ ባለቤቶችን በመቀማመጥ ላይና የብክለትና የመጥፎ ስነ ምግባር ባለቤቶችን በመራቅ ላይ መነሳሳቱና መበረታታቱን እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

