ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።"
Explanation
የመጀመሪያውም:- "በአላህ ማጋራት ነው።" ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፤ እንዲሁም ከአላህ ውጪ የሆነን አካል በተመላኪነቱ ፣ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ አላህ በተለየበት ነገር ላይ ከአላህ ጋር እኩል ማድረግ ማለት ነው።
ሁለተኛው:- "የወላጆችን ሐቅ ማጓደል": ይህም ማንኛውም ወላጆችን ወደ ማወክ የሚዳርግ ንግግርም ይሁን ተግባር መፈፀምና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው።
ሶስተኛው: "ነፍስን ያለ አግባብ ማጥፋት ነው።" ይህም በግፍ ወይም ወሰን በማለፍ መግደል ማለት ነው።
አራተኛው: "(የሚን አልገሙስ) አስማጭ መሀላ ነው።" ይህም እየዋሸ እንደሆነ እያወቀ በውሸት መማል ነው። በዚህም ስያሜ የተጠራበት ምክንያት ሰውየውን ወንጀል ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ ስለምታሰምጠው ነው።
Benefits
ሐዲሡ ውስጥ እነዚህ አራት ወንጀሎች ብቻ መጠቀሳቸው ወንጀልነታቸው ከባድ ስለሆነ እንጂ የቁጥር ገደብ አይደለም።
ወንጀሎች ወደ ትላልቅና ትናንሽ ይከፈላሉ። ትላልቅ የሚባሉት: ማንኛውም አለማዊ ቅጣት የተቀመጠለት ወንጀል ለምሳሌ :- ቅጣቱ በሸሪዓዊ መቅጫ ህግ ውስጥ ያለ (ሑዱድ)፣ መረጋገም ያለበት፤ ወይም እሳት መግባትን የመሰለ አኺራዊ ዛቻ የመጣበት ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው። የክልከላ ደረጃውም ከፊሉ ከከፊሉ ይከብዳል። ትናንሽ ወንጀሎች የሚባሉት ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች ውጪ ያሉት ናቸው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

