Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution. Page 2.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
የጀነትና እሳት ባህሪዎች
አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካ…
የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?
ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?" እነርሱም "ፊታችንን አላበራህልንምን? ጀነት አስገብተህስ ከእሳት አላዳንከንምን?" ይላሉ። ነቢዩ እንዲህ አሉ "የፊቱን ግር…
አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ…
ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ…
ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች።
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: «ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች። በስተሰሜን ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ትገርፋለች። (በዚህም) ውበትና ቁንጅናን ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅናቸው ጨምሮም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶ…
'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እን…
እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዒድ አልአድሓ ወይም በዒድ አልፈጥር ወደ መስገጃ ስፍራ ሲሄዱ በሴቶች በኩል አለፉና እንዲህም አሉ: "እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የ…
አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"» «አቡ ሁረይራም እንዲህ አለ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች…
አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እንዲህ በማለት ወደ ጀነት ላከው። "ወደ ርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" ወደ እርሷ ተመልክቶ በመመለስ እንዲህ አለ፦ "በልቅናህ ይሁንብኝ ስለርሷ ማንኛውም ሰው ቢሰማ ከመግባት ወደኋላ የሚል የለም"…
ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል። ተጣሪም እንዲህ በማለት ይጣራል: "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ቀጥሎ ተጣሪው እንዲህ በማለት…
የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የምድር እሳት ለቅጣት) በቂ ነበረች’እኮ" ተባሉ። እሳቸውም፦ "የጀሀነም እሳት ከምድር እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጋለች። ሁሉም ክፍል የምድር እሳት አምሳያ ሀሩርነ…

