'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነት አይገቡም፤ መዓዛዋንም አያገኙም። የጀነት ሽታዋም (እነሱ ካሉበት) የሆነ ያክል ርቆ ይገኛል።'"
Explanation
የመጀመሪያው አይነት ሰዎች: ሰዎችን የሚመቱበት የከብት ጭራ የሚያክል አለንጋ ይዘው የሚዞሩ ሰዎች ናቸው። እነርሱም ሰዎችን ያለ አግባብ በመምታት የግፈኞች ተባባሪ የሆኑ ፖሊሶች ናቸው።
ሁለተኛው አይነት ሰዎች ደግሞ: በተለምዶ የሴቶች ተፈጥሮ የሆነውን የጥብቅነትንና አይነ አፋርነትን ልብስ ያወለቁ ሴቶች ናቸው።
በተጨባጭ ገላቸው ላይ ልብስ ያለ ቢሆንም በትክክለኛው ግን የተራቆቱ ናቸው። ምክንያቱም እነሱ ቆዳቸውን ግልፅ ለማውጣት ሰውነትን የሚያሳይ ቀጭን ልብስ ነውና የሚለብሱት፤ (ወይ) ውበታቸውን ለማጉላት የተወሰነ ሰውነታቸውን ሸፍነው የተወሰነውን የገለጡ ናቸውና በማለት እነዚህን ሴቶች ገለጿቸው። በአለባበሳቸውና በአረማመዳቸው የወንዶችን ቀልብ ወደነርሱ እንዲያዘነብል የሚያደርጉ፣ ትከሻዎቻቸውንም የሚያወዛውዙ፣ ሌሎችንም እነርሱ ወደ ወደቁበት ጥመት እንዲያዘነብሉ የሚያደርጉ ናቸው። ከነዚህ ሴቶች ባህሪ መካከልም: ጭንቅላታቸው ያዘነበለ የግመል ሻኛ ይመስላል። የፀጉራቸውን መጠን በማሰሪያና በመሳሰሉት በማሰር ያተልቋታል። በግመል ሻኛ የተመሳሰሉት ፀጉራቸውና ጉንጉናቸው ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ ስለሚልና የግመል ሻኛ እንደሚዘነበለው ፀጉራቸውን በሚጎነጎኑት ሳቢያ ወደአንድ ጎን እስኪዘነበል ድረስ ሰበር ስለሚል ነው። ይህን ባህሪ የተላበሱ ሴቶች እነርሱ ላይ ይህ ከባድ ዛቻ አለባቸው። እርሱም ጀነት ላይገቡ፣ ሽታዋንም ላያገኙ፣ ወደርሷም ላይቀርቡ ነው። የጀነት መዓዛ ከሩቅ ስፍራ ነው የሚሸተው።
Benefits
ግፈኞችን በግፋቸው ላይ ማገዝ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ሴቶች ከመገላለጥ፣ ከመራቆት፣ ሀፍረተ ገላን ከሚገልፅ ወይም ቅርፅን ከሚያሳይ ጠባብና ስስ ልብስ መጠንቀቅ እንዳለባቸው።
ሙስሊም ሴቶች የአላህን ትእዛዝ አጥብቀው በመያዝ ላይና አላህን ከሚያስቆጣውና በመጨረሻው ዓለም አሳማሚና ዘውታሪ ቅጣት እንዲገባቸው ከሚያደርጓቸው ነገር እንዲርቁ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ይህ ሐዲሥ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ከሚጠቁሙ ሐዲሦች አንዱ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (በህይወት ዘመናቸው) ያልተከሰተ ሩቅ ጉዳይን ተናገሩ እንደተናገሩትም ተከሰተ።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

