Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution. Page 18.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
ዐቂዳ (እምነት)
እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)
ከአቡ ዓብደላህ ጃቢር ቢን ዐብደላህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: «አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ) በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም -የ…
አላህን በመፍራት፤ ባሪያ እንኳ ቢሾምባችሁ እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። እነሆ! ከናንተ መካከል ከኔ በኋላ የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ማየቱ አይቀርም፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን!
ከአቡ ነጂሕ ዒርባድ ቢን ሳሪየህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ልቦናዎች የራዱበትና አይኖች ያነቡበትን ምክር መከሩን። እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት ልክ የተሰናባችን ምክር ይመስላል። ምከሩን!" አልናቸው። እርሳቸውም: "አላህን በመፍራት፤ ባሪያ እንኳ ቢሾምባችሁ እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ።…
በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው።
ከሙዓዝ ቢን ጀበል - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝንና ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ይንገሩኝ። አልኳቸው። እርሳቸውም: "በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የ…
አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል።
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) አስቦ ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ…
አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አ…
አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።
አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ጥርት ያለ ሙናፊቅ ይሆናል። ከነርሱ መካከል ከፊሉ ያለበት ሰው እስኪተወው ድረስ ከፊል ንፍቅና ይኖርበታል። ሲያወራ ይዋሻል፣ ቃልኪዳን ይዞ ያፈርሳል፣ ቀጠሮ ይዞ ያፈርሳል፣ ሲሟገት (ድንበር ያልፋል) በጥመት ላይ ነው።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አራት (ባሕርያት) በእርሱ ላይ ያለበት ሰው ሙናፊቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ባህሪዎች ውስጥ አንዱ ያለበት ደግሞ እስኪተዋት ድረስ አንድ የሙናፊቅነት ባህሪ ይኖረዋል፦ ሲናገር ይዋሻል፤ ቀጠሮ የያዘ ጊዜ ያፈርሳል፤…

