Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
ነፍስን ማጥራት
የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም።
ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: -ኑዕማን (መስማቱን ለማረጋገጥ) በሁለት ጣቶቹ ወደ ጆሮዎቹ እየጠቆመ፦ "ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱ…
በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉ: "በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።" ኢብኑ ዑመርም እንዲህ ይል ነበር "ስታመሽ ንጋትን አትጠብቅ፣ ስታነጋ ምሽትን አትጠብቅ፣ በጤንነትህ ለበሽታህ ስንቅ ያ…
አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ። ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለው፤ እርዳታ አይንፈገው፤ አያሳንሰው።" ወደ ደረታቸው እየጠቆሙም ሶስት…
ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።
አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት
ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው…
የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለድንገተኛ እይታ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም አይኔን እንዳዞር አዘዙኝ።
ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል
አቢ ማሊክ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰ…
በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ
ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከር…
አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አን…
እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከዚያም ትቷት እንደሄደ ተጓዥ አምሳያ እንጂ ሌላ አይደለሁም።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰሌን ላይ ተኙ። ከተኙበት ሲነሱም ሰሌኑ ጎናቸው ላይ ሰንበር አውጥቷል። እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለርሶ ለስላሳ ፍራሽ ብናዘጋጅሎትስ?" አልን። እርሳቸውም: "እኔና ዱንያ ምን አገናኘን? እኔ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ተ…

