ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: -ኑዕማን (መስማቱን ለማረጋገጥ) በሁለት ጣቶቹ ወደ ጆሮዎቹ እየጠቆመ፦ "ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱ…

