አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"
Explanation
Benefits
ኢብኑ ኻዚን እንዲህ ብለዋል: "ፀጋ ማለት ሰው የሚጣቀምበትና የሚደሰትበት ነገር ነው። ኪሳራ ማለት አንድን ነገር በእጥፍ ዋጋው መግዛት ወይም ከሚገባው ዋጋ ባነሰ መሸጥ ማለት ነው። ሰውነቱ ጤነኛ ሆኖና ቆልፈው ከሚይዙት ወጥመዶችም ነፃ ሆኖ ከዚያም ለመጪው አለም ጥቅሙ ያልለፋ ሰው በንግዱ አለም እንደከሰረ ነው የሚቆጠረው።"
ጊዜያቸው ከማለፉ በፊት ወደ አላህ ለመቃረብና መልካም ለመስራት ጤንነትንና ትርፍ ጊዜን መጠቀም ላይ ጉጉት ሊኖረን እንደሚገባ እንረዳለን።
የአላህን ፀጋ ማመስገን አላህን በመገዛት ላይ በማዋል ነው የሚሆነው።
ቃዲ አቡበከር ቢን አልዐረቢ እንዲህ ብለዋል: «አላህ ለባሮቹ በዋለው የመጀመሪያ ደረጃ ፀጋ ዙሪያ ዑለማዎች የተለያየ ሀሳብ ሰጥተዋል: "ኢማን" ተብሏል፤ "ህይወት" ተብሏል፤ "ጤንነት" ተብሏል፤ የመጀመሪያው አጠቃላዩ ፀጋ ስለሆነ የተሻለውም እርሱ ነው። ህይወትና ጤንነት አለማዊ ፀጋዎች ናቸው። እነዚህ ነገሮች ከኢማን ጋር እስካልተቆራኙ ድረስም ትክክለኛ ፀጋ አይሆኑም። አብዛኛው ሰው እነዚህ ሶስቱም ሲሰጠው ይከስርበታል። ማለትም ትርፉን ያስወግዳል ወይም ይቀንሳል። እረፍት ላይ ከምታዘወትረውና በመጥፎ ከምታዘው ነፍሱ ጋር አብሮ በመቀጠል የአላህን ህጎች ከመጠበቅና አምልኮ ላይ ከመዘውተር የተወ ሰው በርግጥም ከስሯል። ልክ እንደዚሁ ትርፍ (ነፃ) ወቅት ኑሮት ያልተጠቀመበትም ከስሯል። የተጠመደ ሰው ትርፍ (ነፃ) ወቅት ካለው ሰው የተለየ ምክንያት ይኖረዋል። ትርፍ ወቅት ያለው ምክንያት ስለማይኖረው ተጠያቂነት ይጠብቀዋል።»
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

