በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉ: "በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።" ኢብኑ ዑመርም እንዲህ ይል ነበር "ስታመሽ ንጋትን አትጠብቅ፣ ስታነጋ ምሽትን አትጠብቅ፣ በጤንነትህ ለበሽታህ ስንቅ ያዝ፣ በህይወትህ ለሞትህ ስንቅ ያዝ።"»
Explanation
ኢብኑ ዑመርም ይህን ምክር በመመርኮዝ እንዲህ ይል ነበር: ያነጋህ ጊዜ ምሽትን አትጠብቅ፤ ያመሸህ ጊዜ ንጋትን አትጠብቅ፤ ነፍስህን የቀብር ነዋሪ አድርገህ ቁጠራት፤ እድሜ ከጤናና በሽታ አያገልምና። ለበሽታ ዘመንህ ስንቅ ሊሆንህ ዘንድ የጤንነትህን ዘመን በአምልኮ ተቻኮልባት፤ ባንተና በጤንነት መካከል በሽታ ከመጋረዱ በፊት በጤንነት ዘመንህ መልካም ስራዎችን ሸምት፤ የዱንያ ህይወትህን ሸምትባት፤ ከሞት በኋላ የሚጠቅምህን ነገር ዱኒያ ላይ ሳለህ ሰብስብ!
Benefits
ምክርና ጥቆማ እንዲሰጠው ላልጠየቀ ሰው እንኳ በምክርና ጥቆማ መጀመር እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አሳማኝ ምሳሌን በመጥቀስ የማስተማር ስልታቸው ማማሩን እንረዳለን። ይህንንም "በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።" ከሚለው ንግግራቸው የምንረዳው ነው።
ሰዎች ወደ መጪው አለም ባላቸው ጉዞ እንደሚለያዩ እንረዳለን። በዱንያ ጉዳይ ቸልተኛ ከመሆን አንፃር እንደ እንግዳ ከሆነ ሰው ይልቅ እንደ መንገድ አላፊ የሆነ ሰው የበለጠ ቸልተኛ ነው።
ምኞትን ማሳጠርና ለሞት መዘጋጀት መገለፁን እንረዳለን።
ሐዲሡ ከዱንያ ቸልተኛ መሆንንና ዱኒያን ማሳነስን ይጠቁማል እንጂ ሲሳይን መተውና የዱንያን ጥፍጥና መከልከሉን አይጠቁምም።
መልካም ስራ የመስራት አቅምን ከማጣትና በበሽታ ወይም በሞት ከመጋረድ በፊት መቻኮል እንደሚገባ እንረዳለን።
ዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዚህ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምክር ተፅእኖ ስር መውደቁ የርሱን ደረጃ ያስረዳናል።
የአማኞች ሀገር ጀነት ናት። አማኝ ሰው በዱንያ ውስጥ እንግዳ ነው። ጉዞውም ወደ መጪው ሀገር ነው። ቀልቡን በእንግድነት ሀገር ውስጥ በአንዳችም አያንጠለጥልም። ይልቁንም ቀልቡ ወደ ሚመለስበት ሀገር የተንጠለጠለ ነው። በዱንያ ውስጥ ያለው ቆይታ ጉዳዩን ለማስፈፀምና ወደ ሀገሩ ለመመለስ የመሰናዳት ያህል ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

