በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት እና በነቢዩ ሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዓባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት እና በነቢዩ ሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።"
Explanation
የመጀመሪያው: በአላህ ጌትነት መውደድ ነው። ይህም በርሱ ላይ የአላህን ጌትነቱን የሚያስፈርዱ ሲሳይ ማከፋፈልና ሁኔታዎችን መወሰን ሲከሰትበት ልቡ ውስጥ አንዳችም ተቃውሞ አያገኝምም፤ ከአላህ ውጪ ጌታንም አይፈልግም።
ሁለተኛ: በእስልምና ሃይማኖት መውደድ ነው። ይህም እስልምና ላካተታቸው ሀላፊነቶችና ግዴታዎች ልቡን መክፈቱና ከእስልምና መንገድ ውጪ ላለ ሃይማኖት ልቡን አለመክፈቱ ነው።
ሶስተኛ: በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መልክተኝነት መውደድ ነው። ይህም እርሳቸው ይዘውት ላመጡት ነገር ባጠቃላይ ምንም ሳይጠራጠርና ሳያወላውል ልቡን መክፈትና መደሰት፤ የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ የገጠመውን ካልሆነ በቀር ላያደርግ ነው።
Benefits
ሰውነት የምግብና የመጠጥ ጣዕም ጥፍጥና የሚሰማው ጤነኛ ሲሆን ነው። ልክ እንደዚሁ ቀልብ ከአጥማሚ ዝንባሌና ክልክል ስሜቶች በሽታ ሲነፃ የኢማንን ጥፍጥና ያገኛል። ቀልብ ከታመመና ከተጎዳ ግን የኢማንን ጥፍጥና ሳይሆን የሚያገኘው መጥፊያው የሆነ ወንጀልና ዝንባሌ ነው የሚጣፍጠው።
የሰው ልጅ አንድን ነገር ከወደደና መልካም ካደረገው ነገሮች ይገሩለታል። አንድም ነገሩ አይከብደውም። ከርሱ በሚመጣ ነገር ባጠቃላይም ይደሰታል። የሚያስደስተው ነገር ነፀብራቅ ቀልቡን ይቀላቀለዋል። ልክ እንደዚሁ አንድ አማኝ ኢማን ቀልቡ ውስጥ የገባ ጊዜ ጌታውን መታዘዝ ይገራለታል፣ ነፍሱም በዚህ ትደሰታለች፣ እርሷን ማከምም አይከብደውም።
ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ በአላህ ጌትነትና ተመላኪነት መውደድን፣ በመልክተኛውና ለርሳቸው በመታዘዝ መውደድን፣ በሃይማኖቱና ለርሱ እጅ መስጠቱን መውደድን አካቷል።»
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

