አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት።
ከዓብደላህ ቢን መስዑድ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት። ከነርሱ በኋላ ግን የማይሰሩትን የሚናገሩና ያልታዘዙትን የሚሰሩ ምትኮች…

