'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው። ሓያእ (አይነ አፋርነትም) የኢማን አንዱ ክፍል ነው።'"
Explanation
ከኢማን ክፍሎች ውስጥ በላጩና ከፍተኛው ትርጉሙን አውቆ ፣ የሚያስፈርደውን በመተግበር "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው። አላህ አንድና ብቸኛ አምላክ መሆኑንና ለአምልኮ የተገባ ብቸኛ አምላክ መሆኑን ከርሱ ውጪ ያለ ማንም አምልኮ እንደማይገባውም ማመን ነው።
የኢማን ትንሹ ስራ ሰዎችን የሚያውክ የሆነን ነገር ሁሉ ከመንገዳቸው ላይ ማስወገድ ነው።
ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሓያእ (አይነ አፋርነት) የኢማን አንድ ክፍል መሆኑን ተናገሩ። ይህም መልካም ለመስራትና ፀያፍ ለመተው የሚያነሳሳ ባህሪ ነው።
Benefits
ኢማን ንግግርም፣ ተግባርም እምነትም ነው።
አላህን ማፈር ሲባል: አላህ በከለከለህ ስፍራ አለማየቱና ባዘዘክ ስፍራ አለማጣቱን ያስፈርዳል።
ቁጥር መወሳቱ በርሱ ላይ ብቻ መገደቡን አያሲዝም። ይልቁንም የኢማን ተግባራት ከዚህም መብዛታቸውን ይጠቁማል። ዓረቦች ከዛ ቁጥር በላይ ያለን ውድቅ ማድረግ ሳይፈልጉም አንዳንድ ነገሮችን በቁጥር ገድበው ያወሱታል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

