{ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።}
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዙበይር ቢን አልዓዋም እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል: {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} [አትተካሡር: 8] የሚለው አንቀፅ የወረደ ጊዜ ዙበይር እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!
እንመገብ የነበረው ሁለቱን ጥቁሮች ተምርና ውሃ ነው። ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው?" እሳቸውም "እርሱኑ ሳይሆን አይቀርም የምትጠየቁት።" አሉት።
Explanation
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እናንተ በዚህ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ከመሆናችሁም ጋር ስለነዚህ ፀጋዎች ትጠየቃላችሁ። እነዚህ ሁለቱም ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎቹ መካከል ናቸውና።" አሉ።
Benefits
ትንሽም ይሁን ብዙ ፀጋ የትኛውም ባሪያ የትንሳኤ ቀን ስለርሱ የሚጠየቅበት መሆኑን እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

