HadeethEnc · 1.23.0
'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላትን ከመተው አስጠነቀቁ። በሰውዬውና ሺርክና ክህደት ላይ በመውደቅ መካከል ያለው ግርዶ ሶላትን መተው እንደሆነም ተናገሩ። ሶላት ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል ሁለተኛው ማእዘን ነው፣ ሶላት በኢስላም ትልቅ ጉዳይ ነው። ግዴታነቱን አስተባብሎ የተወ ሰው በሁሉም ዑለማእ (የኢስላም ሊቃውንት) ስምምነት መሰረት ክዷል። በስንፍናና ድክመት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተወም እንደዚሁ ከሀዲ ነው። በዚህ ዙሪያ የሶሐቦች ሙሉ ስምምነት እንዳለም ተሰምቷል። አንዳንዴ የሚተው አንዳንዴ የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ ለዚህ ከባድ ዛቻ የተጋረጠ ይሆናል።
03
Benefits
ሶላትና በርሱ ላይ መጠባበቅ ያለውን አንገብጋቢነት እንረዳለን። ሶላት በክህደትና ኢማን መካከል ያለ መለያ ነው።
ሶላትን የተወና ያጓደለ ሰው ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ መምጣቱን እንረዳለን።
ሶላትን የተወና ያጓደለ ሰው ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ መምጣቱን እንረዳለን።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

