ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር ሁሉ መጠበቅ ፈልጌ እፅፈው ነበር። ቁረይሾች እንዲህ በማለት ከለከሉኝ 'ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምትሰማውን ነገር ሁሉ ትፅፋለህን? የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኮ ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ!' ከመፃፍ ተቆጥቤ ይህንን ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳሁ። እሳቸውም በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: ' ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'"
Explanation
እነርሱ የተናገሩትን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገርኳቸው። በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: "ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በደስታም ይሁን በንዴት በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብሆን ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።"
በርግጥ ከፍ ያለው አላህም ስለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም።* እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጂ ሌላ አይደለም።} [አንነጅም:3 -4]
Benefits
ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ሱናን በመጠበቅና በማስተላለፍ ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
አስፈላጊ ከሆነ ጉዳዩን አፅንኦት ለመስጠት ያህል መሀላ ሳንጠየቅም መማል እንደሚፈቀድ።
እውቀትን በጽሑፍ ማስቀመጥ እውቀትን ከሚጠብቁ ዘዴዎች መካከል ዋነኛው መሆኑን እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

