ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው። አይሸኑም፤ ሰገራም አይወጣቸውም፤ አይተፉም፤ አይናፈጡም። ማበጠሪያቸው ወርቅ ነው፤ ላባቸው ሚስክ ነው፤ እጣን ማጤሻቸው ምርጥ መአዛ ያለው እንጨት የ 'ኡሉወቱል አንጁጅ' ነው፤ ሚስቶቻቸው ሑሩል ዒን ናቸው። ጀነት ሲገቡ ልክ እንደ አንድ ሰው አፈጣጠር በአባታቸው አደም ቅርፅ ላይ ሆነው ነው የሚገቡት። ቁመታቸው ስልሳ ክንድ ሆነው ነው የሚገቡት።"»
Explanation
Benefits
ሀሳቦችን ለማስረዳትና ለማብራራት ምሳሌዎችን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: "የጀነት ሰዎች ፂም የሌላቸውና ፀጉራቸውም የማይቆሽሽ ከመሆኑ ጋር ማበጠሪያ ለምን ያስፈልጋቸዋል? መአዛቸው ከሚስክ የበለጠ ምርጥ ሆኖ ሳለ እጣንስ ለምን ያስፈልጋቸዋል? የሚል ጥያቄ ከተነሳ: የጀነት ሰዎች ፀጋ መብላቱም፣ መጠጣቱም፣ መልበሱም፣ ሽቶውም በረሃብ ወይም በጥም ወይም በመራቆት ወይም በመቆሸሽ ህመም ምክንያት የሚጠቀሙት አይደለም። የጀነት ፀጋ የተከታተለ እርካታና የተነባበረ ፀጋ ስለሆነ ነው። የዚህም ጥበብ ዱንያ ላይ ይጣቀሙበት በነበረው አይነት እንዲጣቀሙ ነው። ተብሎ ይመለሳል።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

