Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
በመጨረሻው ቀን ማመን
እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር።
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለት ቀብሮች በኩል አለፉና እንዲህ አሉ ' እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር።' ቀጥለውም እርጥብ ቅጠል በመያዝ ለሁለት ሰነጠ…
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት።
ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት። እርሱም "እኔ አላህና መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደዴ ውጭ ምንም ነገር አላዘጋጀሁም።" አለ። እርሳቸውም "አ…
አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል። እርሷ ጀነት ናት የሚላት እሳት ናት። እኔ ኑሕም ህዝቦቹን እንዳስጠነቀቀው…
ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።
ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ እንዲህ አያሉ ደንግጠው ገቡ: "ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።" አሉና በአውራ ጣታቸውና በጠቋሚ ጣታቸው ክብ አደረጉ። ዘይነብ ቢንት ጀሕሽም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በመካከላችን ደጋጎች…
‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላ…
በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።
ከዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እው…
ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድም…
የጀነት ነዋሪ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ደካማ፣ ዝቅ የሚደረግ፣ በአላህ ላይ ቢምል ግን አላህ መሃላውን እውን የሚያደርግለት የሆነ ሁሉ ነው። የእሳት ነዋሪስ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ልበ ደረቅ፣ ትዕቢተኛና በኩራት የተሞላ ነው።
ከሓሪሣ ቢን ወህብ አልኹዛዒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የጀነት ነዋሪ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ደካማ፣ ዝቅ የሚደረግ፣ በአላህ ላይ ቢምል ግን አላህ መሃላውን እውን የሚያደርግለት የሆነ ሁሉ ነው። የእሳት ነዋሪስ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን?…
ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብ…
ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።
ከበራእ ቢን ዓዚብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።" ይህም አላህ እንዲህ እንዳለው ነው: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብ…
‹አንድ አማኝ የትንሳኤ ቀን ወደ ጌታው ይቀርባል። በርሱ ላይ መሸፈኛውን አኑሮበት ወንጀሎቹን እንዲያምን ያደርገዋል።
ከሶፍዋን ቢን ሙሕሪዝ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ሰውዬ ለኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አለ: "የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለ መመሳጠር ሲናገሩ የሰማሀው ነገር አለን?" እርሱም አለ: "እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹አንድ አማኝ የትንሳኤ ቀን ወደ ጌታው ይቀርባል። በርሱ ላይ መሸፈኛውን አኑሮበት ወ…

