ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ እንዲህ አያሉ ደንግጠው ገቡ: "ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።" አሉና በአውራ ጣታቸውና በጠቋሚ ጣታቸው ክብ አደረጉ። ዘይነብ ቢንት ጀሕሽም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በመካከላችን ደጋጎች እያሉ እንጠፋለን?" አለች። እርሳቸውም "አዎን ፀያፍ የበዛ ጊዜ" አሏት።
Explanation
Benefits
ወንጀልን በማውገዝ ላይና እንዳይፈፀም በመከላከል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ደጋጎች ቢበዙ ራሱ ወንጀሎች በዝተውና ተስፋፍተው እስካልተወገዙ ድረስ አጠቃላይ ጥፋት ይከሰታል።
መከራ ሲመጣ ደጋጎችንም ሆነ መጥፎዎችን አጠቃላይ ሰዎችን ያዳርሳል። ነገር ግን የትንሳኤ ቀን ሲቀሰቀሱ በኒያቸው ላይ ሆነው ይቀሰቀሳሉ።
"ስለቀረበው አደጋ ወዮላቸው ለዐረቦች!" በማለት ዐረቦችን የለዩት ይህን በሚናገሩበት ወቅት በጊዜው የሰለሙት አብዛኛዎቹ እነርሱ ስለሆኑ ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

