እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር።
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለት ቀብሮች በኩል አለፉና እንዲህ አሉ ' እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር።' ቀጥለውም እርጥብ ቅጠል በመያዝ ለሁለት ሰነጠ…

