HadeethEnc · 1.23.0
ቀብር የመጪው ዓለም የመጀመሪያው ማረፊያ ነው። ከቀብር (ቅጣት) ከዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ከርሱ የበለጠ ቀላል ነው። ከቀብር (ቅጣት) ካልዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
የዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነፃ የወጣ ባሪያቸው ከሆነው ከሃኒእ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑሥማን ቀብር ላይ የቆመ ጊዜ ፂሙ እስኪረጥብ ድረስ ያለቅስ ነበር። ለርሱም "ጀነትና እሳት በሚወሱ ጊዜ አታለቅስም። በዚህ ግን ታለቅሳለህን?" ተባለ። እርሱም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ቀብር የመጪው ዓለም የመጀመሪያው ማረፊያ ነው። ከቀብር (ቅጣት) ከዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ከርሱ የበለጠ ቀላል ነው። ከቀብር (ቅጣት) ካልዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።"»
02
Explanation
የአማኞች መሪ ዑሥማን ቢን ዓፋን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቀብር ላይ የቆሙ ጊዜ በእንባቸው ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ ያለቅሱ ነበርና እንዲህ ተባሉ: ጀነትና እሳት ሲወሱ ጀነትን ከመናፈቅ ወይም እሳትን በመፍራት ምክንያት ሳታለቅስ ቀብር ላይ ሲሆን ታለቅሳለህ? እርሳቸውም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር ከመጪው አለም ማረፊያዎች መካከል የመጀመሪያው ማረፊያ እንደሆነ ተናግረዋል። ከቀብር ቅጣት ከዳነና ከተገላገለ ከርሱ በኋላ ያለው ማረፊያ ቀላል ነው። ከቀብር ቅጣት ካልዳነ ደግሞ ከርሱ በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።" ብለዋል አለ።
03
Benefits
ዑሥማን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በጀነት ከተበሰሩት መካከል አንዱ ከመሆናቸውም ጋር የነበራቸው የአላህ ፍራቻ ተገልጿል።
የቀብርና የትንሳኤን ጭንቀት በምናስተሰውስ ጊዜ ማልቀስ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
የቀብር ፀጋና ቅጣት የተረጋገጠ መሆኑን እንረዳለን።
ከቀብር ቅጣት መስፈራራቱን እንረዳለን።
የቀብርና የትንሳኤን ጭንቀት በምናስተሰውስ ጊዜ ማልቀስ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
የቀብር ፀጋና ቅጣት የተረጋገጠ መሆኑን እንረዳለን።
ከቀብር ቅጣት መስፈራራቱን እንረዳለን።
Attribution
[ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

