Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution. Page 29.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የ…
የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ «የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሁለተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የከብት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሶስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ ቀንዳም ሙክት ቁርባን እንዳቀረ…
ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።
ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።
በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)
ከአቡ ኡማማህ ኢያስ ቢን ሠዕለበህ አልሓሪሢይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (…
ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።
ዉዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ ጁሙዓ በመምጣት ኹጥባን ዝም ብሎ ያዳመጠ በዚህኛው ጁሙዓና በቀጣዩ ጁሙዓ መካከል የሰራው ተጨማሪም ሶስት ቀን የሰራው ወንጀል ይማራል።
የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው።
ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን…
በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በአንዳች ነገር ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በአንዳች ነገር ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ። (የትንሳኤ ቀን) መልካም ስራ ካለው በበደሉ ልክ ይቀነስበታል። ለርሱ መልካም ስራ ከሌለው ከበደለው…

