HadeethEnc · 1.23.0
በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"
02
Explanation
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና በሚመለስበትና በስራው የሚመነዳበት በሆነው በመጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ:
የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላህ ማለት፣ ላኢላሃኢለላህ ማለት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ በተጣሉ ሰዎች መካከል ማስማማት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ይህንን ካልፈፀመ ዝምታን ያዘውትር፣ ክፋቱን ይቆጥብ፣ ምላሱን ይጠብቅ።
ሁለተኛ: ጉረቤትን ማክበር፡ ይህም እነሱን ባለማወክና ለነርሱ በጎ በማድረግ ነው።
ሶስተኛ: ለመዘየር የመጣን እንግዳ መልካም በማናገር፣ ምግብ በማብላትና ይህን በመሳሰሉት ማክበር ነው።

03
Benefits
በአላህና በመጨረሻው ቀን ማመን ለሁሉም መልካም ነገር መሰረት ነው። መልካም ተግባራትን በመፈፀም ላይም ያነሳሳል።
ከምላስ ወለምታ መከልከሉን እንረዳለን።
የኢስላም ሃይማኖት የአንድነትና የቸርነት ሃይማኖት መሆኑን እንረዳለን።
እነዚህ ጉዳዮች ከኢማን ክፍሎችና ምስጉን ከሆኑ ስነስርአቶች መካከል መሆናቸውን እንረዳለን።
ንግግር ማብዛት ወደሚጠላ ወይም ወደተከለከለ ነገር ይጎትታል። ሰላም የሚገኘው ከመልካም ውጪ ባለመናገር እንደሆነ እንረዳለን።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares