'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀምረተል ዐቀባህ መወርወሪያ ንጋት ላይ ግመላቸው ላይ ሆነው 'ጠጠር ልቀምልኝ!' አሉኝ። ሰባት ጠጠርም ለቀምኩላቸው። እነርሱም ትናንሽ በጣት መሀል የሚወረወሩ ጠጠሮች ነበሩ። መዳፋቸው ላይ አኑረው እያገላበጧቸውም 'መጠናቸው በነዚህ ልክ ያሉ ጠጠሮችን…

