ጉንጩን የመታ፣ አንገትያውን የቀደደ፣ በድንቁርና ጥሪ የተጣራ ከኛ አይደለም።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ጉንጩን የመታ፣ አንገትያውን የቀደደ፣ በድንቁርና ጥሪ የተጣራ ከኛ አይደለም።"»
Explanation
የመጀመሪያው: ጉንጩን የመታ ነው። ጉንጭን የለዩት በአብዛኛው የሚፈፀመው እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተቀሩትን የፊት ክፍልን መምታትም ክልከላው ውስጥ ይካተታል።
ሁለተኛው: ልብስ ላይ ጭንቅላት እንዲገባበት ተብሎ የሚከፈተውን (አንገትያ) ከትእግስት ማጣት ብዛት መቅደድ ነው።
ሶስተኛው: የድንቁርና ዘመን ጥሪዎችን መጣራት ነው። ለምሳሌ ያህል፦ ወዮልኝ፣ ወይኔ በጠፋው ማለት፣ ሙሾ ማውረድ፣ እየገጠሙ ማለቃቀስና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።
Benefits
በመከራ ላይ መታገስ ግዴታ መሆኑንና አሳማሚ በሆኑ የአላህ ውሳኔዎች ላይ መበሳጨት ክልክል መሆኑን እንረዳለን። የዚህም መገለጫው: ሙሾ በማውረድ ወይም እየገጣጠሙ በማልቀስ ወይም በመላጨት ወይም በመቀዳደድ ወይም ከዚህም ውጪ ያለን በመስራት ነው።
ሸሪዓ ያላፀደቀውን የድንቁርና ዘመን ጉዳዮችን መከተል ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ማዘንና ማልቀስ በአላህ ውሳኔ ላይ ከመታገስ ጋር ስለማይፃረር ችግር የለውም። ማልቀስ አላህ በቅርብ ዘመዶችና ወዳጆች ቀልብ ውስጥ ያደረጋት እዝነት ናት።
ሙስሊም የሆነ ሰው በአላህ ፍርድ መውደድ አለበት። ባይወድ እንኳን መታገስ ግዴታው ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

