የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከጁንዱብ ቢን ዐብደላህ አልቀስሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው። ከናንተ አንዳችሁ በአላህ ጥበቃ ስር ያለውን ሰው በምንም መንገድ አይጉዳ። ያንን የሠራ ሰው የአላህ ቁጣ በእርግጥ ይይዘዋል ከዚያም በአፍጢሙ በጀሀነም እሳት ውስጥ ይደፋዋል።"
Explanation
ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት በመተው ወይም ሰጋጁን በመተናኮልና ሰጋጁ ላይ ወሰን በማለፍ ይህንን ከለላ ከማፍረስ አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመም ይህንን ጥበቃ ስለጣሰ ለብርቱ ዛቻ የተጋለጠ ይሆናል። የአላህን ሀቅ ወሰን ስላለፈም በአላህ ይፈለጋል። አላህም የሚፈልገውን ያገኘዋል፤ ከዚያም በአፍጢሙ እሳት ውስጥ ይደፋዋል።
Benefits
ፈጅር የሰገደን ሰው በሚተናኮል ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ መምጣቱን እንረዳለን።
አላህ ደጋግ ባሮቹን የሚተናኮል ሰውን እንደሚበቀል ተረድተናል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

