የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በአንዳች ነገር ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በአንዳች ነገር ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ። (የትንሳኤ ቀን) መልካም ስራ ካለው በበደሉ ልክ ይቀነስበታል። ለርሱ መልካም ስራ ከሌለው ከበደለው ባልደረባው ወንጀሎች ተወስደው እርሱ ላይ ይደረጋሉ።"»
Explanation
Benefits
ከሰው ሐቆች ጋር የተያያዙን ነገሮች ከጫንቃችን ላይ ለማፅዳት በመቻኮል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
መልካም ስራዎች ሰዎችን በመበደልና በማወክ ይበላሻሉም ፍሬ አልባም ይሆናሉ።
የሰዎች ሐቅ ወደ ባለቤቱ በመመለስ ካልሆነ በቀር አላህ የሚምረው ጉዳይ አይደለም።
ዲናርና ዲርሃም በዱንያ ውስጥ ጥቅምን ለማስገኘት የምንዳረስባቸው መንገዶች ናቸው። በመጪው አለም ግን ለክፍያ ጥቅም ላይ የሚውሉት መልካም ስራዎችና ሀጢአቶች ብቻ ናቸው።
አንዳንድ ዑለሞች ክብርን በመንካት ጉዳይ እንዲህ ብለዋል: "ተበዳዩ ክብሩ እንደተነካ የማያውቅ ከሆነ ማሳወቁ አስፈላጊ አይደለም። ለምሳሌ በአንድ ስፍራ ቢሰድበውና ስለስድቡ ተውበት ቢያደርግ የግድ ሰድቤሃለሁ ብሎ ማሳወቅ አያስፈልግም። ይልቁንም ለርሱ ምህረትን ይጠይቅለታል። ዱዓም ያደርግለታል። ይሰድበው የነበረበት ስፍራ ላይም በመልካም ያወሳዋል። በዚህም የስድቡ ወንጀል ይነሳለታል።"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

