የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።" ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ "በአላህ እምላለሁ! እርሳቸው ሚል በማለት የፈለጉት የምድር ርቀት መለኪያውን ይሁን ወይስ ዐይን መኳያ እቃውን ይሁን ምን እንደፈለጉበት አላውቅም።" ነቢዩ እንዲህም ብለዋል "ሰዎችም እነደየስራቸው መጠን በላብ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከመታጠቂያው ድረስ የሚሆንም አለ፤ ከነርሱ መካከልም ላቡ የሚለጉመው አለ።" ብለው የአላህም መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በእጃቸው ወደአፋቸው ጠቆሙ።»
Explanation
Benefits
የትንሳኤ ቀን ሰዎች በመቆሚያ ስፍራ ላይ እንደየስራዎቻቸው ልክ በጭንቅ ውስጥ እንደሚሆኑ እንረዳለን።
ወደ መልካም ተግባራት መነሳሳቱንና ከመጥፎ ተግባራት ደግሞ ማስፈራሪያ መምጣቱን እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

