የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ በርዛህ አልአስለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"
Explanation
የመጀመሪያው: ህይወቱን በምን እንዳጠፋውና እንዳሳለፈው?
ሁለተኛው: ዕውቀቱን ለአላህ ብሎ ነው የፈለገው? በእውቀቱ ሰርቶበታልን? ማወቅ ለሚገባውስ አስተላልፎታልን?
ሶስተኛው: ገንዘቡን ከየት ነው ያገኘው? ከሐላል ነው ወይስ ከሐራም? ለምንስ አዋለው? አላህን በሚያስደስት ነገር ላይ አዋለው? ወይስ በሚያስቆጣው ነገር ላይ?
አራተኛው: ስለ አካሉ፣ ሀይሉ፣ ጤንነቱ፣ ወጣትነቱ ነው። ምን ላይ ተጠቅሞ እንዳሳለፈው?
Benefits
አላህ በባሮቹ ላይ የዋለው ፀጋ ብዙ ናቸው። ስለነበረበት ፀጋም ይጠይቀዋል። ስለዚህ የአላህን ፀጋዎች እርሱን በሚያስደስት ነገር ላይ ማዋል ይገባዋል።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

