በሙሐመድ ሚስቶች ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታ አሰምተዋል። እነዚህ ሚስቶቻቸውን የሚመቱ ባሎች ምርጦች አይደሉም።
ከኢያስ ቢን ዐብደላህ ቢን አቢ ዙባብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "የአላህን ሴት ባሮች አትምቱ!" ዑመርም ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አሏቸው: "ሴቶች በባሎቻቸው ላይ እያመፁ ነው።" የዛኔም እንዲመቷቸው ፈቀዱ። የነቢዩ -የአላህ ሶላትና…

