ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰማ: "ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።" ዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "የአ…

