HadeethEnc · 1.23.0
የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ሳለን እንዲህ አሉ: "የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።"»
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግንኙነትንና የጋብቻን ጣጣ የቻለን ሰው እንዲያገባ አነሳሱ። ይህም ጋብቻ አይንን ከሐራም ጠባቂና ብልቱንም እጅግ በጣም ጠብቆለት ዝሙት ላይ ከመውደቅ ስለሚከለክለው ነው። የጋብቻን ጣጣ ሳይችል ግንኙነትን የቻለ ሰውም መጾም ይገባዋል። ፆም የብልትን ስሜት እና መጥፎ የዘር ፈሳሽን ይቆርጣልና።
03
Benefits
እስልምና በጨዋነት ምክንያቶች ላይና ከዝሙት መፅዳት ላይ ጥረት ማድረጉን እንረዳለን።
የጋብቻን ጣጣ ያልቻለ ሰው በመፆም መነሳሳቱን እንረዳለን። ፆም ስሜትን ያዳክማልና።
ፆም ከመኮላሸት ጋር የተመሳሰለው: መኮላሸት ማለት የሁለቱን ፍሬዎች ደምስር መቀጥቀጥ ማለት ነው። ሁለቱ ፍሬዎች በመወገዳቸውም የግንኙነት ፍላጎት ይወገዳል። ልክ እንደዚሁ ፆምም የግንኙነትን ስሜት ያደክማል።
የጋብቻን ጣጣ ያልቻለ ሰው በመፆም መነሳሳቱን እንረዳለን። ፆም ስሜትን ያዳክማልና።
ፆም ከመኮላሸት ጋር የተመሳሰለው: መኮላሸት ማለት የሁለቱን ፍሬዎች ደምስር መቀጥቀጥ ማለት ነው። ሁለቱ ፍሬዎች በመወገዳቸውም የግንኙነት ፍላጎት ይወገዳል። ልክ እንደዚሁ ፆምም የግንኙነትን ስሜት ያደክማል።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

