ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።
Explanation
አንድ የአንሷር ሰውዬም እንዲህ አለ: እስኪ ንገሩኝ የባል ወንድም፣ የወንድሙ ልጅ፣ አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ የእህቱ ልጅና የመሳሰሉት ባታገባ ኖሮ ልታገባቸው የሚፈቀዱላት የባል ቅርብ ዘመዶች ቢገቡስ ይፈቀዳልን?
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "ሞትን እንደምትጠነቀቁት እርሱንም ተጠንቀቁት! ከባል ዘመዶች ጋር ገለል ብሎ ማሳለፍ ለሃይማኖት ፈተናና ጥፋት የሚመራ ነው። ከአባቱና ከልጆቹ ውጪ ያሉ የባል ቅርብ ዘመዶችን መከልከል ከሌላው ባዳ ወንድ የበለጠ የተገባ ነው። ይህም ከሌላ ባዳ ጋር ለብቻ ከምታሳልፍበት ጊዜ ይልቅ ከባል ቅርብ ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ እድሉ የበዛ ስለሆነ ከሌላው በበለጠ ከርሱ ጋር መጥፎ ነገር መከሰቱ ስለሚገመትና ያለምንም አውጋዥ ወደ ሴቷ መድረስና ከርሷ ጋር ለብቻ ማሳለፍ ስለሚችል ፈተና የመከሰት እድሉም የሚመች ነው። በተለምዶ የባል ወንድም የወንድሙ ሚስት ብቻዋን እያለች መግባት ቸል የሚባል ጉዳይ ስለሆነ ፈተና መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ከባዳ ወንድ ጋር ለብቻ ማሳለፍማ የሚጠነቀቁት ጉዳይ ነው። ከርሱ በተቃራኒ ከባል ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ አፀያፊነትና የሚያስከትለው ችግር ግን ከሞት ጋር ይመሳሰላል።
Benefits
ይህ ክልከላ የሴቷ ቅርብ ዘመዶች ያልሆኑን የባል ወንድምንና ቅርብ ዘመዶቹን ጨምሮ ባዳ ወንዶችን ባጠቃላይ የሚጠቀልል ነው። (ባል በሌለበት) መግባቱ ብቻ ከርሷ ጋር መገለልን ማስፈረዱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
መጥፎ ነገር ላይ መውደቅን በመፍራት ብዙሃን ስህተት ላይ የሚወድቁበትን ስፍራ መራቅ ይገባል።
ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «የቋንቋ ምሁራን ባጠቃላይ እንደተስማሙት "አሕማእ" ማለት የባል ቅርብ ዘመዶች ናቸው። አባቱ፣ አጎቱ፣ ወንድሙ፣ የወንድሙ ልጅ፣ የአጎቱ ልጅና የመሳሰሉት ማለት ነው። "አኽታን" ማለት ደግሞ የሚስት ቅርብ ዘመዶች ናቸው። "አስሃር" የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም የሚውል ስም ነው።»
የባል ዘመድ ከሞት ጋር አመሳስለው የመግለፃቸው ምስጢር:- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ዐረቦች የሚጠሉትን ነገር በሞት ይመስሉታል። የመመሳሰሉም መልክ ከባል ዘመድ ጋር ወንጀል ከተፈፀመ በዲን በኩል እንደሞት ነው፤ ወንጀል ከተፈፀመም ከባል ዘመድ ጋር ተገልላ ያሳለፈችው የመወገር ግዴታ ስላለባት ትሞታለች፤ ባል ቅናቱ ለፍቺ ከገፋፋውም ከባሏ መለየቷ ለሴቷ ጥፋት ነው።»
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

