Prophetic Hadeeth Encyclopedia
Search and read verified Prophetic hadeeth translations, explanations, benefits, categories and source attribution. Page 8.
Search the Hadeeth Encyclopedia
Smart instant results tolerate minor spelling mistakes, with every filter in one place.
አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየ…
አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ "አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላ…
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር። እንዲህም ይሉን ነበር: "አንዳችሁ አንድ ጉዳይ ያሰበ ጊዜ ግዴታ ከሆነ ሶላት ውጪ ሁለት ረከዓ ይስገድና እንዲህ ይበል:…
የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም።
ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ ንጉስ ነበር። ለርሱም ጠንቋይ ነበረው።
ከሱሀይብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ «ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ ንጉስ ነበር። ለርሱም ጠንቋይ ነበረው። (ጠንቋዩ) ያረጀ ጊዜም ለንጉሱ እንዲህ አለው: "እኔ አርጅቻለሁ። ጥንቆላ የማስተምረው አንድ ህፃን ልጅ ወደ እኔ ላክልኝ።" ንጉሱም የሚያስተምረውን ህፃን ልጅ ወደርሱ ላከለት። ልጁም ወደ…
ከጀናባ አስተጣጠብ ሁኔታ
የአማኞች እናት ከሆነችው ከመይሙና (ረዲየላሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መታጠቢያ ውሃ አቀረብኩኝና በልብስም ሸፈንኩላቸው። እርሳቸውም በእጃቸው ላይ አፈሰሱና ሁለት እጃቸውን አጠቡ። ቀጥለው በቀኝ እጃቸው ግራ እጃቸው ላይ እያፈሰሱ ብልታቸውን አጠቡ። በእጃቸውም መሬቱን መቱና ጠረጉት። ቀጥለውም አጠቡት። ተጉመጠመጡ፣…
እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'
በዑሥማን ነፃ የወጣ የሆነው ሑምራን እንዳስተላለፈው እሱ "ዑሥማንን የውዱእ እቃ እንዲያመጡላቸው ሲጣሩ አየ። (የውዱእ እቃ ሲቀርብላቸውም) ከእቃው ውሀ በእጆቻቸው ላይ አፈሰሱ። እያፈሰሱም ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን በውዱእ እቃ ውስጥ አስገብተው ውሀ ዘገኑና በዚያው ተጉመጠመጡ አፍንጫቸው ውስጥም ውሀውን አስገብተው ድጋሚ አስወጡ። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ፣ ሁለት እጆቻቸውንም እስከ ክርኖቻቸው ሶስት ጊዜ አ…
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር። ከዚያም በእጃቸው ፀጉራቸውን ይፈለፍላሉ። (የፀጉራቸው) ቆዳ በውሃ መራሱን እስከሚያስቡ ድረስም እየፈለፈሉ በጭ…
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።
በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።
ከእናትችን ዓኢሻና ዐብደላህ ቢን ዓባስ - (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የሞት መልዐክ በአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የወረደ ጊዜ ፊታቸው ላይ ጨርቃቸውን ጣል ማድረግ ጀመሩ ፤ ሲያፍናቸው ደግሞ ይገልጧት ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ 'በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።'…
ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእ…

