የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።»
Explanation
መጀመሪያ: ከአፋቸው ወይም ከአፍንጫቸው አንዳች ነገር ወጥቶ አብሯቸው የተቀመጠውን ላለማወክ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ ያኖራሉ።
ሁለተኛ: ድምፃቸውን ይቀንሱ ነበር። ከፍም አያደርጉትም።
Benefits
አንድ ሰው ያስነጠሰ ጊዜ ከርሱ አንዳች ነገር ወጥቶ አብሮ የተቀመጠውን እንዳያውክ ልብስን ወይም መሀረብና የመሳሰሉትን አፍና አፍንጫ ላይ ማኖር እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሲያስነጥሱ ድምፅን ዝግ ማድረግ የሚፈለግ ጉዳይ ነው። ይህም ስነ-ስርዓትን ከሚያሟሉና ከመልካም ስነ‐ምግባር የሚመደብ ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

